በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቻይናው ርዕደ መሬት አደጋ የተሰወሩትን ሰዎች ማፈላለግ ቀጥሏል


በደቡባዊ ምስራቅ ቻይና ሲሿን ክፍለ ግዛት፣ ሉዲንግ በተባለው ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎች ወደ ሌላ ስፍራ እየሰፈሩ ነው።
በደቡባዊ ምስራቅ ቻይና ሲሿን ክፍለ ግዛት፣ ሉዲንግ በተባለው ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎች ወደ ሌላ ስፍራ እየሰፈሩ ነው።

ቻይና ውስጥ ባላፈው ሰኞ ከደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ ጋር በተያያዘ የተሰወሩትን 26 ሰዎች የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ማፈላለግ የያዙ መሆኑ ሲነገር ቢያንስ 74 የሚሆኑን ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የቻይና መንግሥት ዜና ማሰራጫ የሆነው ሲሲቲቪ እንደዘገበው በሬክተል ስኬል 6.8 በሆነው የርዕደ መሬት አደጋ መውጫ አጥተው የቀሩ በርካታ ሰዎችን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞቹን እያፈላለጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከአደጋው ጋር ተያይዞ በደቡባዊ ምስራቅ ቻይና ሲሿን ክፍለ ግዛት፣ ሉዲንግ በተባለው ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት 300 የሚደርሱ ነዋሪዎች ወደ ሌላ ቦታ የሰፈሩ ሲሆን ከመካከላቸው 29 የሚሆኑት የቆሰሉ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ርዕደ መሬቱ ከደረሰበት ስፍራ፣ 200 ኪሎ ሜትሮች ርቀት በምትገኘው የክፍለ ግዛቲቱ ዋና ከተማ ድረሰ ዘልቆ መሰማቱም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG