በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቤጂኒግ ኦሎምፒክ ላይ የተጣለው እቀባ የተጨማሪ ሃገሮችን ትብብር ይጠይቃል


ዩናይትድ ስቴትስ በቻይናው የቤጂንግ የክረምት ኦሎምፒክ ላይ የጣለቸው የዲፕሎማሲ እቀባ ውጤታማ እንዲሆን ብዙ ሃገሮች ተባባሪ መሆን ይኖርባቸዋል ሲሉ ባለሙያዎች አሳሰቡ፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ ሃገሮች ከቻይና ጋራ ባላቸው የምጣኔ ሀብት ትስስር የተነሳ ተባባሪ ላይሆኑ ይችላሉ ብለዋል፡፡

እስካሁን የባይደን አስተዳደርን ውሳኔ ተከትለው የእቀባው ተባባሪ የሆኑ ሃገሮች እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያና ኒውዚላንድ ናቸው፡፡

የሚቀጥለው የበጋ ኦሎምፒክ አዘጋጅ የሆነችው ፈረንሳይ ተባባሪ እንደማትሆን አሳውቃለች፡፡

ጀርመን እና ኖርዌም ውሳኔውን ገና ያላሳወቀው የአውሮፓ ህብረትን እየተጠባበቁ መሆኑን ገለጸዋል፡፡

ከቻይና ጋር ጥብቅ የንግድ ትስስር እንዲኖራቸው የሚፈልጉ እንደ ፖላንድና ሀንጋሪ የመሳሰሉ የምስራቅ አውሮፓ ሃገሮች ውሳኔውን ለመቀበል ስለሚቸግራቸው የአውሮፓ ህብረት አቋም ምን ሊሆን እንደሚችል ግልጽ አለመሆኑ ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG