በያዝነው ዓመት ያለፉት አምስት ወራት ውስጥ ብቻ፣ በዩናይትድ ስቴትስ፣ ቁጥራቸው ከ670 የሚበልጡ አዳጊዎች እና ሕፃናት፣ በጥይት ተመትተው መገደላቸውን፣ ቫዮለንስ አርካይቭ የተባለው ገለልተኛ የመረጃ አሰባሰቢ ቡድን ይፋ አድርጓል።
የተጠቀሰው አኀዝ፣ በአዳጊዎች እና ሕፃናት ላይ በመሣሪያ የሚፈጸመው ግድያ፣ በከፍተኛ ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱን እንደሚጠቁም ተመልክቷል፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ፣ አንዲት የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባል የነበሩ እናት፣ ይህን ችግር ለመቅረፍ፣ ከማኅበረሰቡ ጋራ በመተባበር በመሥራት ላይ ይገኛሉ።
ካሪና ባፍራድዚያን ያጠናቀረችውን የዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።