በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከ50 በላይ የሚሆኑ የቺቦክ ሴቶች በሕይወት መኖራቸውን የሚያሳይ ቪድዮ ተገኘ


ከ50 የሚሆኑ ከሁለት አመታት በፊት ከቺቦክ ናይጀርያ የተጠለፉት ሴት ተማሪዎች ያሉበት ቪድዮ ባለፈው እሁድ ከታየ በኋላ የናይጀርያ መንግሥት ከቦኮ ሐራም ጋር ለመነጋገር እየሞከረ እንደሆነ ገልጿል።

ከነሱም በርካታ መሞታቸውን ጽንፈኛው ቡድን ተናግሮ በህይወት ላሉት የእስረኞች ልውውጥ እየጠየቀ ነው ተብሏል።

ትላንት እሁድ ዩቱብ ላይ የወጣው ቪድዮ ሻሽ ያደረጉ ስጋት የሚታይባቸው ወጣት ሴቶች ጭምብል እጥልቆ ወታደራዊ ልብስ የለበሰ ሰው አጠገብ ተቀምጠውና ቆመው ያሳያል። በሀውሳ የሚናገረው ሰው የናይጀርያ መንግሥት በአቡጃ፣ በሌጎስና በማይዱጉሪ የያዛቸውን የቦኮሐራም አባላት እንዲለቅ ጥሪ አቅርቧል። ቦኮ ሐራም ከዚህ ቀደምም ጠይቆ ነበር የሚሉ ተቆርቋሪዎች የናይጀርያ መንግሥት ለተጠለፉት ልጆች ሲል ከቦኮ ሐራም ጋር መደራደር አለበት ይላሉ።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያይዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ከ50 በላይ የሚሆኑ የቺቦክ ሴቶች በሕይወት መኖራቸውን የሚያሳይ ቪድዮ ተገኘ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG