በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ግጭት የልጆችን የመማር ዕድል ማኰሰሱን የረድኤት ድርጅቶች ገለጹ


የሱዳን ግጭት የልጆችን የመማር ዕድል ማኰሰሱን የረድኤት ድርጅቶች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:38 0:00

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት(ዩኒሴፍ) በቅርቡ እንዳስታወቀው፣ የሱዳኑ ጦርነት፥ ቁጥራቸው ቢያንስ 450 ሺሕ የሚደርሱ ሕፃናትን ከመኖሪያቸው ሲያፈናቅል፣ በ10ሺሕዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ወደ ጎረቤት አገሮች ለስደት ዳርጓል።

ለስደት የተዳረጉት እነኚኽ ሕፃናት፣ ከትምህርት ገበታቸው መነጠላቸውን ያመለከቱት የረድኤት ድርጅቶች አክለውም፣ በትምህርት ገበታቸው ሊያቆያቸው የሚችል ዕድል በሌለበት፣ ሕፃናቱ ለሕገ ወጥ ብዝበዛ፣ ያለዕድሜ ጋብቻ እና በለጋነት ለውትድርና ምልመላ

የመጋለጥ ከፍ ያሉ አደጋዎች እንደተጋረጡባቸው ተናግረዋል።

ሄንሪ ዊልከንስ ከሱዳን ድንበር አቅራቢያ ከምትገኘው የቻዷ ቦሮታ ያደረሰንን ዘገባ አሉላ ከበደ ወደ ዐማርኛ መልሶታል።

XS
SM
MD
LG