በሐዲያ ዞን የሾኔ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኞች፣ ከግንቦት እስከ ሐምሌ ድረስ ያሉት የሦስት ወራት ደመወዛቸው እንዳልተከፈላቸው ገልጸው፣ ሆስፒታሉ አገልግሎት ማቆሙን ተናግረዋል፡፡
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዲሬክተር ዶር. መሐመዲን አሕመድ፣ ለተከታታይ ወራት የታጎለውን የሠራተኞች ደመወዝ በተመለከተ፣ ለበላይ አካላት ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠቅሰው፣ “አፋጣኝ ምላሽ ግን አልተሰጠንም፤” ብለዋል፡፡
የአሜሪካ ድምፅ፣ ከሐዲያ ዞን አስተዳደር እና ከዞኑ ፋይንናንስ ጽሕፈት ቤት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት፣ ባለሥልጣናቱ ስልኮቻቸውን ስለማያነሡ እንዲሁም “በአካል ቢሮ ድረስ ካልመጣችኹ መልስ አንሰጥም፤” በማለታቸው በዚኽ ዘገባ ለማካተት አልተሳካም፡፡