በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሰላም ድርድር ካለተጨባጭ ውጤት ተጠናቀቀ


ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ

እአአ ከ2013 ጀምሮ የእርስ በርስ ጦርነት የሚካሄድባት የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሰላም ድርድር ያለተጨባጭ ውጤት አብቅቷል። ዛሬ የተጀመረው የሰላም ንግግር ላይ አንድም አማጺ ቡድን አልተጋበዘም፣ ተቃዋሚዎችም አንገኝም ብለዋል።

እአአ በ2020 መጨረሻ በአወዛጋቢ መንገድ በድጋሚ የተመረጡት ፕሬዚዳንቱ ፎስቲን ቱዋዴራ ሪፐብሊካዊ የእርቀ ሰላም ውይይት ተብሎ የተሰየመው ውይይት ይካሄዳል ብለው ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ከዚያም ተከትሎ ነው በድንገት በዚሁ በመጋቢት ወር ውስጥ ከተቃዋሚዎች እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ጋር ንግግር እንደሚከፈት ያስታወቁ ሲሆን የውይይቱ አጀንዳ እና ተጨባጭ ግቡ ምን እንደሆን ግልጽ እንዳልነበር ተዘግቧል።

የአካባቢው ኤክስፐርቶች በበኩላቸው የውይይቱ አላማ የድጋፍ እጁን እየሰሰበሰበ ያለውን ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማረጋጋት ነው ይላሉ።

XS
SM
MD
LG