በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ያሊ ለአፍሪካ ወጣቶች ምን ጠቀመ?


ያሊ ለአፍሪካ ወጣቶች ምን ጠቀመ? ስመኝሽ የቆየ ከአምባሳደር ግሪንፊልድ ንግግር በተጨማሪ ኢትዮጵያን ወክለው በያሊ የተሳተፉ ወጣቶችን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች። 

ያሊ ለአፍሪካ ወጣቶች ምን ጠቀመ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:05 0:00


ኮቪድ 19 እና የአየርን ንብረት የመሳሰሉ ድምበር ተሻጋሪ ቀውሶች ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን በፈተኑበት በዚህ ወቅት የአፍሪካ ወጣቶች ከአህጉራቸው አልፈው ለዓለም ህዝብ ተስፋ መሆናቸውን በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሆኑት ሊንዳ ቶምሰን ተናግረዋል።

አምባሳደር ግሪን ፊልድ ይህን ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት በየአመቱ የሚዘጋጀውና በእንግሊዝኛ ስሙ ምኅፃር - ያሊ ተብሎ የሚጠራው፣ የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ልምድ የመለዋወጫ መድረክ የተመሰረተበትን አስረኛ አመት ክብረ በዓል አስመልክቶ በድህረ ገፅ አማካኝነት በተዘጋጀ ጉባኤ ላይ ነው።

የዛሬ አስር አመት - በ2003 ዓ.ም ፣ የአፍሪካ የወደፊት መሪዎች ይሆናሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው ወጣቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ተመርጠው ለልምድ ልውውጥ ወደ አሜሪካ ሲላኩ አምባሳደር ግሪንፊልድ በላይቤሪያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ ነበር። የመጀመሪያ ተሳታፊ ከነበሩት ወጣቶች መሀል ላይቤሪያን ወክለው የሄዱትን መርጠው የላኩትም እሳቸው ናቸው። በመክፈቻውም ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

ከአስር አመት በኃላ በድህረ ገፅ ተገኝተው በተለያዩ አመታት የያሊ ተሳታፊ ለነበሩ ወጣቶች ንግግር ሲያደርጉም ለአመታት ከያሊ ጋር የዘለቀው ቁርኝታቸው በብዙዎች የያሊ እናት አንዳንዴም የያሊ አያት የሚል ቅፅል እንዳሰጣቸው አምባሳደር ግሪን ፊልድ ተናግረዋል።

"ልክ እንደ ጥሩ እናት ወይም ጥሩ አያት ስለ እናንተ ሳወራ፣ ከናንተ ጋ በመቆራኘቴ ልቤ በኩራት ይሞላል። ስለምትሰሯቸው ትልልቅ ስራዎች ስሰማ ከሚሰማኝ የበለጠ ሊያኮራኝ የሚችል ነገር የለም።"

ያሊ በአስር አመት ጉዞው 115 ወጣቶችን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ወደ አሜሪካ በማምጣት የልምድ ለውውጥ እንዲያደርጉ አስችሏል። በተለያዩ የትስስር መድረኮች አማካኝነትም ከ 21 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ሲኖሩት ከ ግማሽ ሚሊዮን በላይ አባላት እንዳፈራም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ከነዚህ በተለያየ የሙያ መስክ ተሰማርተው ባሳዩት ውጤት የአፍሪካ የወደፊት አመራር ይሆናሉ በሚል ተስፋ ተጥሎባቸው በ2008 ዓ.ም. ወደ አሜሪካ መጥተው ከነበሩ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች መሃል ዲና አንተነህ አንዷ ናት።

ዲና በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ እናቶችና ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የሚያግዝ ተቋም ከፍታ ዝቅተኛ ገቢ ያለውን ማህበረሰብ ታገለግላለች። ሴቶች በኢኮኖሚ እራሳቸውን እንዲችሉም ታግዛለች። የያሊ

ቆይታዋን ጨርሳ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰች በኃላም ለተመራቂ ተማሪዎች የስራ ፈጠራና የሙያ ማዳበሪያ ስልጠና ለመስጠት ከአሜሪካ ኤምባሲ የገንዘብ ድጋፍ አግኝታለች።

ሌላው በያሊ ተሳታፊ የነበረ ወጣት አብርሃም እንድሪያስ ነው። በአሁኑ ወቅት ግሪን አግሮ ሶሊዩሽን የሚባል አነስተኛ እርሻ ላይ የተሰማሩ ገበሬዎችን ከቴክኖሎጂ ጋር የሚያስተዋውቅ ተቋም ውስጥ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሆኖ ያገለግላል። አብርሃም ያሊ ላይ በመሳተፉ ያገኘውን ጥቅም እንዲህ ይገልፀዋል።

አብርሃም አክሎ ያሊ በግል ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በአህጉሩ ለሚገኙ ወጣቶች ትስስር መፍጠር ትልቅ መድረክ መሆኑ የተሻለ የአንድነት እንደሚፈጥር ያምናል።

የያሊን አስረኛ አመት ክብረ በዓል አስመልክቶ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረገት አምባሳደር ግሪንፊልድም አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት፣ የወደፊት ስልጣን ተረካቢ የሆኑት ወጣቶች አዳዲስ የአመራር ስልቶችን በመቀየስ መጪው ትውልድ የሚጋፈጣቸውን ችግሮች ማስወገድ እንዲችሉ ነው።

"ከወረርሽኙ በፊት አፍሪካ በዓለም ላይ ፈጣን እድገት ያለው ኢኮኖሚ ሊኖራት የቻለው እንደ እናንተ ያሉ የሀገራቸው የወደፊት ተስፋ እና ስኬት ላይ አስተዋፅኦ በሚያደርጉና አብረውን ለኖሩ ችግሮች አዳዲስ መፍትሄ በሚያመጡ ወጣቶች ምክንያት ነው። "

ባለፉት አስር አመታት ውስጥ በያሊ ተሳታፊ የነበሩት በርካታ ወጣቶች ዛሬ በትላልቅ የአመራር ቦታዎች ላይ ይገኛሉ፣ ሌሎች ደግሞ በስራቸው ዓለም አቀፍ እውቅናን አግኝተዋል። ለምሳሌ 5 የያሊ ተሳታፊ የነበሩ የአፍሪካ ወጣቶች በመንግስት ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ እንደሚገኙ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይጠቅሳል። ከሶማሊያ ተሳታፊ የነበረች ወጣትም ወለደ ትጥቅ ትግል እንዲገቡ ተደርገው የነበሩ ህፃናትን ከውትድርና በማውጣት መልሰው እንዲቋቋሙ ላደረገችው ጥረት በ2011 ዓ.ም. ለኖቤል የሰላም ሽልማት ታጭታ ነበር።

ለአሜሪካ ድምፅ ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ፣ ዋሽንግተን ዲሲ

XS
SM
MD
LG