በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኮሮናቫይረስ በሕጻናት እና ታዳጊዎች ላይ አስከፊ የሆነ ህመም ያመጣል” ሲዲሲ


U
U

የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠሪያ ተቋም ሲዲሲ አርብ ዕለት ባወጣው ሪፖርት “ኮሮናቫይረስ በሕጻናት እና ታዳጊዎች ላይ አስከፊ የሆነ ህመም ያመጣል” ሲል አስታወቀ፡፡

ካለፈው ሰኔ ወር ማገባደጃ እስከ ነሃሴ አጋማሽ ድረስ፣ በተዛማችነቱ አስጊ የሆነው ዴልታ የተሰኘው ቫይረስ ስርጭት መጨምሩን እና በዚህ ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡ ህጻናት እና ታዳጊዎች ቁጥር፣ በ5 እጥፍ ማደጉንም አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ ለታዳጊዎች የኮቪድ-19 ክትባት መጀመሩን ተከተሎ በተሰራው ጥናት ያልተከተቡ ታዳጊዎች በቫይረሱ የመያዛቸው መጠን በ10 እጥፍ አይሎ መገኘቱም ተጠቁሟል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ድሬክተር “ኮቪድን ለመከላከል የሚደረገው ፍልሚያ ገና ብዙ ይቀረዋል” ሲሉ ዛሬ ሰኞ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅቱ ድሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የደቡብ እስያ አገሮች ኔፓል ላይ ለሚያደርጉት የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ከሮም ባስተላለፉት መልዕክታቸው ፣ “የወረርሹ ተሞክሮ እንደሚያሳየው የትኛውም አገር ቢሆን ትኩረቱን ከኮቪድ ላይ ሊያነሳ አይችልም፡፡ ችላ ማለት በራሱ የቫይረሱ ያህል አደገኝነት ይኖረዋል፡፡ በንቃት መከታተላችንን መቀጠል ይኖርብናል፡፡” በማለት አሳስበዋል፡፡

“ወረረሽኙ አሁን ባለበት መጠን ዳግመኛ እንዳይመጣ” ማድረግ ይኖርብናል ያሉት ድሬክተሩ “ከ 1 እስከ 2ከመቶ ድረስ ብቻ ነዋሪዎቻቸውን ያስከተቡ አገሮች መኖራቸውን ጠቅሰው እንዲህ ያለ አድልዎም ዳግመኛ መፍቀድ አይኖርብንም” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG