አዲስ አበባ —
በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤትና በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ በምርጫ-2007 እንዳይወዳደሩ እገዳ ተጥሎባቸው የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ ስድስት ዕጩዎች በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ እግዱ ተነስቶላቸዋል።
ፍርድ ቤቱ ውሣኔውን ተግባራዊ እንዲሆን ተዕዛዝ ሰጥቷል።
ትዕዛዙ ግን እስከ ዛሬ ተግባራዊ እንዳልተደረገ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡