የካሜሩን የጦር ኃይል በናይጄሪያው ሽብርተኛ ቡድን በቦኮ ሐራም ቁጥጥር ሥር የነበሩ ከ300 በላይ ታጋቾች አስለቅቋል።
የጦር ኃይሉ ካሜሩንን ከናይጄሪያ እና ከቻድ ጋር በሚያዋስናት የድንበር አካባቢ "አልፋ" በሚል ስያሜ ባካሄደው አንድ ሳምንት የፈጀ ዘመቻ ብዛት ያላቸው የናይጄሪያው ቦኮ ሐራም ታጣቂዎችን መግደሉን አስታውቋል።
ያስለቀቃቸውን ታጋቾች በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ወደሚገኝ የጦር ሠፈር ወስዶ ማስፈሩንም አመልክቷል። ሞኪ ኤድዊን ኪንድዜጋ ከያውንዴ ያስተላለፈው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል።
ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች።
መድረክ / ፎረም