በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ቦኮኻራም ተዳክሟል አስጊነቱ እንዳለ ነው" ተመድ


"ቦኮኻራም ተዳክሟል አስጊነቱ እንዳለ ነው" ተመድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:49 0:00

"ቦኮኻራም ተዳክሟል አስጊነቱ እንዳለ ነው" ተመድ

በማዕከላዊ አፍሪካ የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ በቅርቡ የቻድ ሀይቅ አካባቢ ያሉ አገሮችን ህዝቦች የአኗኗር ሁኔታ ለመቃኘት ወደዚያው አቅንተዋል፡፡ ይህን አካባቢ ቦኮ ኻራም ለዓመታት ሲያጠቃው የቆየ ሲሆን ብዙ የመሰረት ልማቶችን ከጥቅም ውጭ አድርጓቸዋል፡፡

ፍራንሶስ ልዎንሴኒ ፎል፣ በማዕከላዊ አፍሪካ ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ልዩ ተወካይ ናቸው፡፡

ባላፉት አምስት ወራት ውስጥ፣ የጂሃዲስቱ ቡድን ቦኮ ኻራም፣ ከአካባቢው እየተመናመነ መምጣቱን ይናገራሉ፡፡

እሳቸው በቦታው የተገኙትም ከዚሁ ጋር በተያያዘ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ እንዲህ ብለዋል ፎል

“በተባበሩት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የተላኩት የቦኮሃራም ተዋጊዎች ይንቀሳቀሱባቸው በነበሩባቸው አካባቢዎች ያሉት የማህበረሰብ አባላት መልሶ ለመቋቋም የሚያስፈልጋቸውን ነገር እንዳለ ለመገምገም ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት፣ በአካባቢው ያሉ የአክራሪ ቡድኖችን በማስወገድ አካባቢውን ወደ ዘላቂ ሰላም ለመመለስ የተደራጁና፣ የአካባቢው አገራት የመሰረቱትን፣ ወታደራዊ ህብረት፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲደግፍ ማስተባበር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ካሜሩንን፤ ናይጄሪያን፣ ኒጀርን በመጎብኘት መልሶ ማቋቋምና ድህነትን መቀነስ ላይ ማተኮር የሚቻልበትን መንገድ እየተመለከትኩ ነው፡፡”

ቤኒንን ጨምሮ፣ ለአገራቱ የጦር ህብረት ወታደሮችን ያዋጡ አገራት፣ ካሜሩን ናይጄሪያና ኒጀር ናቸው፡፡

ፎል እንደሚሉት፣ የተባበሩት መንግሥታት የልማት መርሃ ግብሩ፣ ካሜሩንን ናይጄሪያና ቻድን የሚያገናኝ መንገድ በመስራት፣ የሰዎችንና ሸቀጦችን ነጻ እንቅስቃሴ ለመፍጠር፣ ገንዘብ ማሰባሰብን ያካትታል፡፡

የድርጅቱ የልማት ፕሮግራምም የአካባቢው ሰዎች፣ ዛፎችን እንዲተክሉ ያበረታታል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅትም፣ የተፈናቀሉ ሰዎች፣ እንደ ልደት የምስክር ወረቀትና፣ የመሳሰሉትን ሰነዶች በማዘጋጀት፣ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ያግዛል፡፡ ሴቶች ንግድ እንዲጀምሩ፣ የገንዘብ እገዛ ያደርጋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት፣ ወደ 40 ሚሊዮን ከሚጠጋው የቻድ ሀይቅ ዙሪያ ሰዎች ውስጥ፣ አብዛኞቹ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን፣ ከነዚህም ከፊሎቹ፣ ለድህነት የተጋለጡት፣ በቦኮ ኻራም ጥቃት መሆኑን ይገልጻል፡፡

ሚድ ጂያዋ ባክሪ፣ ከናይጄሪያና ከቻድ ጋር የሚዋሰነው የካሜሩን ግዛት፣ አስተዳዳሪ ናቸው፡፡ ሰላማዊ ዜጎች የተሻለ ህይወት እንዲፈጠርላቸው፣ የካሜሩንን ባለስልጣናትና የተባበሩት መንግሥታትን እርዳታ እየጠየቁ ነው፡፡

ባክሪ እንዲህ ይላሉ

“ ቦኮ ሀራም ባደረሳቸው ጥቃቶች ፣ ለ10 ዓመታት የተዳከመው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ አሁን ቀስ በቀስ እየተነሳ ነው፡፡ ባለፉት አምስት ወራት ዉስጥ ሰላማዊ ዜጎችና ነጋዴዎች በካሜሩን፣ ናይጄሪያና ቻድ መካከል ከሸቀጦቻቸው ጋር በነጻነት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡”

ባክሪ ጨምረው እንደገለጹት፣ በአካባቢው ሰላም የሰፈነ ይመስላል፡፡

የካሜሩን ወታደሮ ከናይጄሪያ ጋር በሚያዋስነው የሰሜን ድንበር ሽብርተኝነትን እየተዋጉ ነው፡፡

ናይጄሪያውያንም የጅሃዲስቶቹ ቡድን መጠነ ሰፊ ጥቃት ቢኖር በሚል፣ ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ በተጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡

የካሜሩን መንግሥት በቦኮኻራም የወደመውን፣ የመሠረተ ልማት መልሶ ለመገንባት 300 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን ይገልጻል፡፡

አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች፣ ትምህርት ቤቶችን፣ የውሃ ጉድጓዶችን፣ የመጻዳጃ ሥፍራዎችን፣ ገበያዎችን፣ ሆስፒታሎችን የመገንባቱ ሥራ መጀመሩንም ጠቅሷል፡፡

ከካሜሩን፣ ከቻድ፣ ከኒጀር እና ናይጄሪያ የተውጣጡ ባለሥልጣናት፣ ባለፈው መስከረም 28፣ በካሜሩና ዋና ከተማ ያውንዴ ውስጥ በመሰብሰብ፣ በቦኮ ኻራም የወደመቱን አካባቢዎች መልሰው ለመገንባት ተስማምተዋል፡፡

ባለሥልጣናቱ የቦኮኻራም መሪ አቡባካር ሺካኡ መሞቱ ባለፈው ግንቦት ከተገለጸ ወዲህ የቻድ ሀይቅ አካባቢዎች ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለሱን አስታውቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ እስካሁንም ድረስ ያለው ሥራ አጥነት በርካታ ወጣቶችን ወደ ጅሃዲስቱ ቡድን እንዳይገፋፋቸው ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል፡፡

ምክንያቱም አሁንም ድረስ ከአካባቢው ወጣቶችን መመልመሉን እንደቀጠለ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG