በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካምቦዲያው የተቃዋሚ መሪ ኬን ሦካ እሥር


የካምቦዲያው የተቃዋሚ መሪ ኬን ሦካ ለእሥር ከተዳረጉ - ባለፈው እሁድ 18ኛ ወራቸውን ይዘዋል።

ሦካ የታሠሩት ከፖለቲካ ጋር በተያያዘና ከሃገሪቱ ሕግ ውጭ ነው ሲሉ፡ ሌሎች የተቃዋሚ መሪዎች ይከራከራሉ።

የካምቦዲያ ብሄራዊ መድህን ፓርቲ መሪው ኬን ሦካ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የታሠሩት የሃገር ክህደት እና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በማሤር የካምቦዲያን መንግሥት ለመገልበጥ ሞክረዋል የሚሉ ክሶች ቀርበውባቸው ነው። ከሳሾቻቸው እስካሁን ያቀረቡባቸው ማስረጃ ደግሞ ለፖለቲካ ሥራቸው ከዩናይትድ ስቴትስ እርዳታ እንደሚያገኙ በአደባባይ የተናገሩበትን ቪዲዮ ነው።

ሦካ ለአንድ ዓመት ከታሠሩ በኋላ በዋስ የተለቀቁ ቢሆንም አሁንም ከቁም እሥር ባላነሰ በፍርድ ቤት ቁጥጥር ሥር ይገኛሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG