በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለጥያቄዎ መልስ፣ አቶ ግዛው ለገሠ እና አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ


ኢትዮጵያን ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ካለፉ በኋላ በአገሪቱ የተከተሉት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች በጥልቀት እየተገመገሙ ነው።

ደጋፊዎቻቸው አስገኙ በሚሏቸው የኢኮኖሚ ዕድገትና በአፍሪቃ መሪነት ሚናቸው ላይ በማተኮር ሲያወድሱ ተቃዋሚዎች ደግሞ በኢትዮጵያ መልካም አስተዳደርን አልተከተሉም፤ ይልቁንስ የፖለቲካ ቅርሣቸው ለአገሪቱ የማይሽር ጠባሣ ነው ይላሉ።

በ “ለጥያቄዎ መልስ” ዝግጅት ቀጥሎ የሚቀርቡ ሁለት ምሁራን እነዚህን ሃሣቦች ያስተናግዳሉ። አቶ ግዛው ለገሠ ቀድሞ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ በውጭ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር ከ1991 እስከ 1995 የኢትዮጵያ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና ዋና ፀሐፊ የነበሩ፣ በአቶ መለስ የፖለቲካ ቅርስ ዙሪያ የአድማጮችን ጥያቄ ይመልሳሉ።

የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ትዝታ በላቸው ነች። ዝግጅቱን ያዳምጡ፡፡


please wait

No media source currently available

0:00 0:35:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG