በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትና ዴሞክራሲ፤ ለ«ጥያቄዎ መልስ» ከፕሮፌሰር አድነው አዲስ ጋር፤


ዴሞክራሲ እንዲጸናና ስር እንዲሰድ፣ የግለስብ፣ የመጻፍ የመናገር ሃሳብ የመለዋወጥ መብትና የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት፣ የተደራጀና ነጻ የፖለቲካ ተቃዋሚ፣ እንዲሁም ገለልተኛና ነጻ ፍርድ ቤቶች መኖር አለባቸዉ ዴሞክራሲ እንዲጸናና ስር እንዲሰድ፣ የግለስብ፣ የመጻፍ የመናገር ሃሳብ የመለዋወጥ መብትና የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት፣ የተደራጀና ነጻ የፖለቲካ ተቃዋሚ፣ እንዲሁም ገለልተኛና ነጻ ፍርድ ቤቶች መኖር አለባቸዉ

ዴሞክራሲ እንዲጸናና ስር እንዲሰድ ከተፈለገ፣ ሶስት አስፈላጊ መብቶች መከበር እንዳለባቸዉ በሉዊዚያና የቱሌን ዩኒቨርሲቲ የአሜሪካ ህገ መንግስትና የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ህጋጋት ፕሬፌሰር አድነዉ አዲስ ለቪኦኤ ”ለጥያቄዎ መልስ” ፕሮግራም ገለጹ። እነዚህም፣ የመጻፍ፣ የመናገር፣ ሃሳብን የመለዋወጥ ነጻነት ለግለሰብም ሆነ ለመገናኛ ብዙሃን ማጎናጸፍ፣ ሁለተኛዉ የተደራጀና ነጻ የፖለቲካ ተቃዋሚ መኖር ሲሆን፣ ሶስተኛዉ ገለልተኛ የሆኑ ፍርድ ቤቶችና ዳኞች መቋቋማቸዉ ነዉ ብለዋል።

ሶስቱም ነጻነቶች አንድ ዋና ዓላማ አላቸዉ። ይሕዉም የጊዜዉ መንግስት በህግ እንዲያስተዳድር፣ ህገ መንግስቱን እንዳይጥስ፣ ሰብአዊ መበቶችን እንዳይገፍና፣ የሚያጸድቃቸዉ ፖሊሲዎች በይፋ ወጥተዉ እንዲገመገሙ የሚያደርጉ ናቸዉ ብለዋል። የፕሬስ ነጻነት፣ የፍርድ ቤትና የዳኛ ነጻነት ከሌለ እንደማይከበር፣ የተደራጀ ገለልተኛና ነጻ የሆነ የፖለቲካ ተቃዋሚ ከሌለ ደግሞ የፕሬስ ነጻነት መከበሩ የመነመነ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ስለዚህ እነዚህ መብቶች የተጣመሩና የዴሚክራሲ ዋና መቆሚያ ምርኩዞች ናቸዉ ብለዋል ፕሮፌሰር አድነዉ አዲስ።

ለዝርዝሩ ”ለጥያቄዎ መልስ” ዝግጅታችንን ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG