በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ዴሞክራሲ ጉዳይ በሁለተኛው ዘመነ-ኦባማ


ወይዘሪት ብርቱካን ሚደክሳ
ወይዘሪት ብርቱካን ሚደክሳ

ፕሬዚደንት ኦባማ በሁለተኛው የአስተዳደር ጊዜአቸው በአፍሪካ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር መስፋፋት ያግዙ ይሆናል ተባለ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:28:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
ባራክ ኦባማ በመጀመሪያዎች አራት ዓመታት የአሜሪካ ፕሬዚደንትነታቸው የአስተዳደራቸው ፖሊሲ የተጠበቀውን ያህል በአፍሪቃ ዴሞክራሲን ለማስፈን እንዳልረዳ ብዙዎች አፍሪቃዊያን ይተቻሉ።

በተለይም ልክ እንደተመረጡ በጋና ዋና ከተማ አክራ ለአፍሪካ መንግሥታት ያደረጉት ንግግር መልካም አስተዳደርን እንደሚያግዙ ያመላከተ ቢሆንም ባንፃሩ ባለፉት አራት ዓመታት በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮች መስፋፋትና ለአምባገነን መሪዎች የሚሰጠው ድጋፍም እንደተጠናከረ የሚናገሩ አፍሪቃዊያን ያማርራሉ።

ሆኖም በርካታ የፕሬዚደንቱ ፖሊሲ ደጋፊዎች በአገር ውስጥ ከባድ የኢኮኖሚ፣ የጤናና የማኅበራዊ ደህንንትን የመሳሰሉ ችግሮችን መፍታት ስለነበረባቸው የተፈለገውን ያህል ለአፍሪካ ትኩረት ባይሰጡም ቀድሞ የነበሩ የጤናና የሰብዓዊ እርዳታዎች እንደቀጠሉ በመግለፅ ይከራከራሉ።

ፕሬዚደንት ኦባማ በሁለተኛው የአስተዳደር ዘመናቸው ለአገራቸው ጥቅም ከመሥራትም ባሻገር በታሪክ በበጎ እንዲታወሱ ለአፍሪካ ዴሞክራሲ ገንቢ ግብዓት ሊያበረክቱ እንደሚችሉ ይናገራሉ።

በጥያቄዎ መልስ ዝግጅታችን አድማጮች በዚህ ርዕስ ዙሪያ ላነሷቸው በርካታ ጥያቄዎች መልስ የሰጡን የቀድሞዋ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደክሳ ዩናይትድ ስቴትስ ዘላቂ ጥቅሟን ማስከበር የምትችለው ከአምባገነን መሪዎች ይልቅ ለህዝብ ሰብዓዊና ፖለቲካዊ ልዕልና በመቆም ነው ይላሉ።

ሙሉውን ዝግጅት ያድምጡ።
XS
SM
MD
LG