በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካሊፎርኒያው ገዥ ሥልጣናቸው ላይ ይቆያሉ


ጋቪን ኒውሰም
ጋቪን ኒውሰም

በዩናይትድ ስቴትስ ምዕራባዊ ክፍለ ግዛት በካሊፍሮኒያ የሚገኙ የዴሞክራቲክ ፓርቲ መራጮች የክፍለ ግዛቱን ገዥ ጋቪን ኒውሰምን ከሥልጣን ለማንሳት የተደረገውን ጥረት አልተቀበሉትም፡፡

ኒውሰም ከሥልጣን እንዲነሱ በተጠራው ምርጫ የካሊፎርኒያው ገዥ ከሥልጣን እንዲነሱ ትልፈጋላችሁ ወይስ አትፈልጉም በሚለው አማራጭ በትናንትናው እለት ድምጽ የሰጡ ወደ 70 ከመቶ የሚጠጉ መራጮች “አንፈልግም” ሲሉ እንዲነሱ እንፈልጋለን ያሉት 30 ከመቶ ብቻ ሆነዋል፡፡

ድጋሚ ምርጫው የተጠራው ኒውሰም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመከላከል የንግድ ድርጅቶችና ትምህር ቤቶች እንዲዘገቡ በማድረግ ያወጧቸውን ህጎች በተቃወሙ የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎችና አባላት ነው፡፡

ከፕሬዚዳንት ባይደን ጀምሮ ፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ ፣ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ሌሎች ከፍተኛ የዴሞክራቲ ፓርቲ ባለሥልጣናት የምርጫውን ዘመቻ እንዲያሸንፉ ረድተዋቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG