በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰፋፊ እርሻዎችና የዜጎች የምጣኔ ኃብት ተሳትፎ ሙግቶች


ጎጀብ
ጎጀብ

ባሳለፍንው ሳምንት አጋማሽ ቦንጋ ከተማ አቅራቢያ በጎጀብ ቀበሌ የሚገኝ 350 ሔክታር የግል እርሻ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥቃት ደረሰበት።

“በመሬታችን ላይ ጭሰኞች ሆንን” ሲሉ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች፤ በቆሎ ሙዝና አናናስ የሚመረትበት ባለቤትነቱ ሆራይዘን ፕላንቴሽን በመባል የሚታወቅ በሼክ ሞሀመድ አል-አሙዲ ባለቤትነት የሚንቀሳቀስ እርሻን አቃጠሉ፣ ምርት አወደሙ፣ ትራክተሮች፣ ኮምባይነሮችና ሞተር ብስክሌቶች በእሳት አጋዩ።

ለሕዝቡን ቁጣ ምን አስነሳው? በአካባቢው የሚኖሩና ለድኅንነታቸ በመሥጋት ስማቸውን ያልጠቀሱ ነዋሪ “ጥያቄው መጀመሪያ ሲነሳ የደመወዝ ጥያቄ ነው፤ ከዚይም የቦታ ጥያቄ ነው” ሲሉ በአካባቢው ነዋሪዎች የመሬት ይዞታና ተጠቃሚነት ዕሮሯቸውን አብራርተዋል።

“በራሳችን መሬት ጭሰኛ ሆነን የሚከፈለን ስድስት መቶ ብር ነው” ብለዋል።

መሬቱ ከቀደመው የደርግ መንግሥት አንስቶ በመንግሥት እርሻ ልማት የነበረና፤ አሁን ለግል የእርሻ ልማት የተላለፈ መሆኑን ከነዋሪዎችና ሌሎች ምንጮች ለመረዳት ችለናል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሰፋፊ እርሻዎችና የዜጎች የምጣኔ ኃብት ተሳትፎ ሙግቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:07 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG