በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቡሩንዲ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ እንዲዘጋ አዘዘች

ቡሩንዲ - በሃገሯ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ቢሮ እንዲዘጋ አዛለች። ዋና ጽሕፈት ቤቱ ጂኒቫ የሆነው የድርጅቱ ቃል አቀባይ ራቪና ሻምዳሣኒ ስለዚሁ ሲናገሩ፣ ጉባዔው በቡሩንዲ ያለውን ቢሮ እንዲዘጋ የሚጠይቀው ደብዳቤ የደረሰው በትላንትናው ዕለት ነው።

ቡሩንዲ - በሃገሯ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ቢሮ እንዲዘጋ አዛለች። ዋና ጽሕፈት ቤቱ ጂኒቫ የሆነው የድርጅቱ ቃል አቀባይ ራቪና ሻምዳሣኒ ስለዚሁ ሲናገሩ፣ ጉባዔው በቡሩንዲ ያለውን ቢሮ እንዲዘጋ የሚጠይቀው ደብዳቤ የደረሰው በትላንትናው ዕለት ነው።

ሻምዳሣኒ ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ የማዕከላዊ አፍሪካ አገልግሎት ዛሬ እንደተናገሩት፣ “በቡሩንዲ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማድረግ ከመንግሥት ጋር ተባብረን የመሥራት ፍላጎት እያለን ይህ ዕርምጃ መወሰዱ አሳዝኖናል” አሁንም ቢሆን የቡሩንዲን መንግሥት በጉዳዩ ላይ ማነጋገራችን ይቀጥላል” ብለዋል።

የቡሩንዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የተባበሩት መንግሥታት ምንጮች በገለጹት መሠረት፣ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ቢሮውን ዘግቶ እንዲወጣ የተሰጠው ጊዜ ሁለት ወራት ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ካውንስሉ ኃላፊ በያዝነው ዓመት መጀመሪያ ላይ በሰጡት አስተያየት ቡሩንዲን የገለጿት፡ “በአሁኑ ወቅት የሰው ልጆች በገፍ የሚታረዱባት ሀገር” ሲሉ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG