በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ውስጥ በተደረመሰ ህንፃ ሰዎች ሞቱ


ፎቶ ፋይል፦ ናይሮቢ፤ ኬንያ
ፎቶ ፋይል፦ ናይሮቢ፤ ኬንያ

ኬንያ ውስጥ ዛሬ ከዋና ከተማዪቱ ወጣ ብላ በምትገኘው ኪርጊቲ ከተማ፣ አንድ ባላ ብዙ ፎቅ ህንፃ ተደርምሶ ቢያንስ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ሲነገር ከአደጋው ጋር ተያይዞ የተሰወሩ በርካታ ሰዎችን ፍለጋ መቀጠሉ ተመልክቷል፡፡

ለህንፃው የመደርመስ አደጋ መንስኤው ግልጽ አለመሆኑን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አስታውቋል፡፡

እንዲህ ዓይነቱ አደጋ ደካማ ቁጥጥር፣ ሙስና፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎች በሚታይበት በናይሮቢና በተለያዩ ቦታዎች ተዘውትሮ የሚታይ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ ገለጿል፡፡

XS
SM
MD
LG