በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእንግሊዝ እንደራሴዎች ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊሄድ ነው


የእንግሊዝ እንደራሴዎች ግንቦት ሰባት የፍትህና የነፃነት ንቅናቄ ይባል ከነበረው ተቃዋሚ ቡድን መሪ በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሄዱ ተገልጿል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ - ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ - ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የእንግሊዝ እንደራሴዎች ግንቦት ሰባት የፍትህና የነፃነት ንቅናቄ ይባል ከነበረው ተቃዋሚ ቡድን መሪ በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሄዱ ተገልጿል፡፡

የፓርላማው አባላት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙት በመጭው የአውሮፓ ወር፤ ፌብሩዋሪ እንደሚሆን ዘ ኢንዲፔንዳንት የሚባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ወደ እንግሊዝ የፖለቲካ ስደተኛ ሆነው የገቡት ከሰላሣ ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ መሆኑን የጋዜጣው ዘገባ ጠቁሞ ላለፉት ስድስት ወራት የሚገኙት ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻቸውን ተነጥለው ታስረው እንደሆነ አመልክቷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ የሚመራው በፓርላማው የሰብዓዊ ጉዳዮች ቡድን ምክትል ሊቀመንበር ጀረማይ ኮርቢን እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ይህንኑ የፓርላማውን አባላት ጉዞ እንደሚያውቁ አንድ ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ለአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰብ የጠበቀ ቅርበት ያላቸው ሰው ለቪኦኤ ገልፀው የእንደራሴዎቹ ጉዞ ተሣክቶ አቶ አንዳርጋቸውን ይዘው ይመለሣሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG