ብሪታንያ በሩስያ ላይ 23 ሩስያውያን ዲፕሎማቶች ማባረርን ያቀፈ የምላሽ እርምጃ መውሰድዋን አስታውቃለች። በሶቭየት ህብረት ዘመን የነበረ ለምት የሚዳርግ የነቭ ኤጀንት የቀድሞ የሩስያ ሰላይ ሰርገይ ስክሪፓልንና ልጃቸው ዩልያን ለመመረዝ እንዴት በብሪታንያዋ ሳልስበሪ ከተማ ሊደርስ ቻለ? ለሚለው ጥያቄ ሩስያ ምላሽ ባለመስጠትዋ ነው እርምጃው የተወሰደው።
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ትሬሳ ሜይ ስለ ውሳኔው የገለፁት በታችኛው የብሪታንያ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ነው። መንግሥታቸው ከጠላታዊ ተግባር ለመከላከል የሚያስችል ህግ እንደሚያረቅና አዲስ ፀረ ስለላ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚያስብበትም ጠቁመዋል።
ከብሪታንያ እንዲወጡ የታዘዙት ሩስያውያን ዲፕሎማቶች የአንድ ሳምንት ጊዜ ተስጥቷቸዋል። ይህን ያክል ብዛት ያላቸው ሩስያውያን ዲፕሎማቶች ከብሪታንያ ሲባረሩ በ47 ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። ሩስያ በመመረዙ ተግባር ውስጥ እጄ የለበትም ብላለች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ