ዋሺንግተን ዲሲ —
ባለፈው ዓመት ሶልስበሪ ውስጥ በሰርጌ ስክሪፓል ላይ ለደረሰው ጥቃት ተጠያቂዎች የሆኑት ሁለቱ ሩስያውያን ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው፣ ቴሬሳ ሜይ ለሩስያው መሪ እንዳሳሰቡ፣ ዛሬ ዐርብ ከቢሯቸው ይፋ የሆነው መግለጫ አመልክቷል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ሜይ አስተያየት የተሰማው፣ ኦሳካ ጃፓን በሚካሄደው፣ የጂ20 ጉባዔ ጎን ከፕሬዚደንት ፑቲን ጋር በተገናኙበት ወቅት ነው።