በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በብራዚል ውርጃን የሚያግደውን ረቂቅ ሕግ በመቃወም ሰልፍ ተደረገ

በብራዚል ውርጃን ወንጀል የሚያደርገውን የሕግ ረቂቅ በመቃወም በርካቶች ኮፓካባና የባሕር ዳርቻ ትላንት እሁድ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።
በብራዚል ውርጃን ወንጀል የሚያደርገውን የሕግ ረቂቅ በመቃወም በርካቶች ኮፓካባና የባሕር ዳርቻ ትላንት እሁድ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።

በብራዚል ውርጃን ወንጀል የሚያደርገውን የሕግ ረቂቅ በመቃወም በርካቶች ኮፓካባና የባሕር ዳርቻ ትላንት እሁድ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።

በረቂቅ ሕጉ መሠረት 22 ሳምንትና ከዛም በላይ የሆነውን ጽንስ ማስወረድ እንደ ነፍስ ማጥፋት ተቆጥሮ እስከ 20 ዓመታት የሚደርስ የእስር ቅጣት ያስከትላል።

አሁን ባለው ሕግ በብራዚል ውርጃ መፈጸም ከአንድ እስከ ሶስት ዓመታት በእስር ያስቀጣል።

በአስገድዶ መደፈር ወይም እርግዝናው ለእናቲቱ ሕይወት አስጊ ከሆነ ግን ውርጃ ይፈቀዳል።

“በማሕጸናችንና በሰውነታችን ላይ የምናዘው እኛ ብቻ መሆናችንን ለዓለም ለማሳየት ወጥተናል” ያለች አንዲት ሰልፈኛ ”መንግስት በሰውነታችን ጉዳይ ጣልቃ መግባት የለበትም” ስትል አክላለች፡፡

ረቂቅ ሕጉ በመላ ሃገሪቱ በገጠመው ተቃውሞ ምክንያት እስከ መጪው ዓመት ድረስ ለድምጽ እንደማይቀርብ ተነግሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG