በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቦትስዋናው ፕሬዚዳንት ለአፍሪካ መሪዎች መልዕክት አስተላለፉ


ፕሬዚዳንት ኢያን ካማ
ፕሬዚዳንት ኢያን ካማ

ሥልጣናቸውን በሰዓቱ ለመልቅቅ የወሰኑት የቦትስዋናው ፕሬዚዳንት፣ “አመራሩን አንለቅም” ለሚሉ የረዥም ዘመናት የአፍሪካ መሪዎች መልዕክት ማስተላለፋቸው ተገለፀ።

ሥልጣናቸውን በሰዓቱ ለመልቅቅ የወሰኑት የቦትስዋናው ፕሬዚዳንት፣ “አመራሩን አንለቅም” ለሚሉ የረዥም ዘመናት የአፍሪካ መሪዎች መልዕክት ማስተላለፋቸው ተገለፀ።

ፕሬዚዳንቱ በዚህ ውሳኔቸው መጀመሪያ እንደ ዚምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮቤርት ሙጋቤ፣ ቀጥሎም እንደ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ለመሳሰሉ፣ ሥልጣን ላይ ሙጭጭ ለሚሉ የአፍሪካ መሪዎች ነው መልዕክት ያስተላለፉት ተብሏል።

በዚሁ መሠረት ሥልጣን መልቀቅ የርሳቸው ተራ ነውና፣ ፕሬዚዳንት ኢያን ካማ ልክ ከአሥር ዓመት በኋላ፣ በመጪው ቅዳሜ ሥልጣኑን ለምክትል ፕሬዚዳንቱ ለሞከገዊቲ ማሲሲ እንደሚያስረክቡ ተገልጿል።

ቦትስዋና ብዙውን ጊዜ በነፃና ሀቀኛ ምርጫ በማካሄድ በተለይም ከነፃነት በኋላ በከፍተኛ ሙስናም የማትታማ አገር መሆኗ ይነገርላታል።

የፕሬዚዳንቱ ቃል-አቀባይ ጄፍ ራመካ እንደገለጹት፣ ፕሬዚዳንት ከሃማ ነፃነትና እኩልነት የሰፈነባት አገር ትተው ነው ከሥልጣን የሚወርዱት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG