በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

117ኛው የቦስተን ማራቶን በቦምብ ተመታ፤ ፕ/ ኦባማ መግለጫ ሰጡ

ከ MBZ TV (ኤምቢዚ ቴሌቪዥን) ከተገኘ የቪድዮ ፋይል የተወሰደው ይህ ምሥል በቦስተን ማራቶን የፍፃሜ መሥመር አባባቢ ከደረሱት ሁለት ፍንዳታዎች ተወዳዳሪዎችን ተመልካቾች ሲሸሹ ያሣያል፡፡ ሚያዝያ 7/2005 ዓ.ም April 15, 2013.
ከ MBZ TV (ኤምቢዚ ቴሌቪዥን) ከተገኘ የቪድዮ ፋይል የተወሰደው ይህ ምሥል በቦስተን ማራቶን የፍፃሜ መሥመር አባባቢ ከደረሱት ሁለት ፍንዳታዎች ተወዳዳሪዎችን ተመልካቾች ሲሸሹ ያሣያል፡፡ ሚያዝያ 7/2005 ዓ.ም April 15, 2013.

ዛሬ በተካሄደው የቦስተን ማራቶን ፍፃሜ መሥመር ላይ በደረሱ ፍንዳታዎች ሦስት ሰዎች ሞቱ፡፡ ከመቶ በላይ ተጎዱ፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ የቦስተኑን ማራቶን ፍንዳታ ተከትሎ በዋይት ሃውስ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ - ሚያዝያ 7/2005 ዓ.ም
ፕሬዚዳንት ኦባማ የቦስተኑን ማራቶን ፍንዳታ ተከትሎ በዋይት ሃውስ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ - ሚያዝያ 7/2005 ዓ.ም

ቀጥተኛ መገናኛ

ዛሬ በተካሄደው 117ኛው የቦስተን ማራቶን ፍፃሜ መሥመር ላይ በደረሱ ሁለት ፍንዳታዎች ሦስት ሰዎች ሞቱ፡፡

ከመቶ ሰው በላይ ሰው መቁሰሉና መጎዳቱም ታውቋል፡፡

በከተማይቱ ሌላ ክፍል ውስጥ በሚገኘው የጆን ኤፍ ኬኔዲ ቤተ መፃሕፍት ውስጥ በደረሰ ፍንዳታም የእሣት ቃጠሎ ተነስቷል፡፡

ሌሎች ሦስት ያልፈነዱ መሣሪያዎች መገኘታቸውና አንዱም ከቦስተን ወጣ ብሎ በሚገኘው ኒውተን ከተማ ውስጥ መሆኑን ስለምርመራው ሂደት ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡ ባለሥልጣናት ማምሻውን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ የቦስተኑን ማራቶን ፍንዳታ ተከትሎ በዋይት ሃውስ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተው እንደጨረሱ
ፕሬዚዳንት ኦባማ የቦስተኑን ማራቶን ፍንዳታ ተከትሎ በዋይት ሃውስ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተው እንደጨረሱ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለጋዜጠኞች በሰጡት በቀጥታ የተላለፈ አጭር መግለጫ የጥቃቱን አድራሽ ወይም አድራሾች /ሰዎች ወይም ቡድኖች/ ተከታትለው እንደሚይዙ ቃል ገብተው ተጠያቂዎች “…ፍትሕን በምሉዕ ክብደቷ ያገኛሉ...” ብለዋል፡፡ እንደሚሰጣቸው አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ጥቃቱን ማን እንዳደረሰና ለምን እንዳደረሰ ገና እንደማያውቁ ገልፀዋል፡፡ ጥቃቱ የሽብር ይሁን ወይም ሌላ፤ በሃገር ውስጥ የተቀነባበረ ይሁን ከውጭ የተላከ ጥቃት እና ሌላም ዝርዝር ጉዳይ አልተናገሩም፡፡

ፕሬዚዳንቱ በተጨማሪም በመላ ዩናይትድ ስቴትስ የተጠንቀቅ ደረጃው ከፍ እንዲልና የቦስተኑም አደጋ በአስቸኳይ እና በቅርበት እንዲጣራ ለሃገር ውስጥ ፀጥታ ሚኒስትራቸውና ለፌደራሉ የምርመራ ቢሮ ኃላፊዎች ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ከማሣቹሴትስ ገዥና ከቦስተን ከንቲባ ጋር መነጋገራቸውን ስለሁኔታው ለአሜሪካ እንደራሴዎችም መልዕክት ማስተላለፋቸውንና በዚህ የአደጋ ጊዜ ዴሞክራቶች ወይም ሪፐብሊካን አለመሆናቸውን፤ ይልቅ ሁሉም አብረው የሚቆሙ አሜሪካዊያን መሆናቸውን ያሳሰቧቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከዓመታዊው የቦስተን ማራቶን በተጨማሪ ዛሬ ለከተማይቱ የአርበኞች ቀን ሕዝባዊ በዓል ነው፡፡

ፍንዳታው ሲደርስ የማራቶኑ ውድድር ፈፃሚዎች ወደ ፍፃሜው መሥመር እየተቃረቡ የነበረ ቢሆንም በፍንዳታው ምክንያት 117ኛው የቦስተን ማራቶን ወዲያው ተቋርጧል፡፡

ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡
የ117ኛው የቦስተን ማራቶን ተወዳዳሪዎች ከሃፕኪንተን-ማሣቹሴትስ ሩጫቸውን እንደጀመሩ፤ ሚያዝያ 7/2005 ዓ.ም /April 15, 2013/
የ117ኛው የቦስተን ማራቶን ተወዳዳሪዎች ከሃፕኪንተን-ማሣቹሴትስ ሩጫቸውን እንደጀመሩ፤ ሚያዝያ 7/2005 ዓ.ም /April 15, 2013/

(የቪድዮ ፋይሎችንና ተጨማሪ ፎቶዎችን በዋናው ገፅ ላይ ከዜናው ሥር ካለው መድብል ይመልከቱ፡፡)
XS
SM
MD
LG