በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የሞተው ልጄ ሞቷል፤ ያሉትን መልሱልኝ” ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ


ፎቶ ፋይል፡ በቢሾፍቱ በእሬቻ በዓል ላይ የሞተ ወጣት የቀብር ሥነ ስርዓት(መስከረም 3/2009)

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው በምስራቅ ሸዋ ዘን ቦሰት ወረዳ የሚገኙ ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ የተባሉ እናት አንድ ልጃቸው እንደተገደለ ሁለቱ እንደታሰሩና አንዱ በእጅጉ መደብደቡን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ለስድስት ወር አስቸኳይ ጊዜ ከታወጀ አንድ ወር ሊሞላው ጥቂት ቀናት ይቀሩታል። ይህ ዐዋጅ ይፋ ከተደረገ በኋላ ሰዎች ከየቦታው እየተለቀሙ እንደሚታሰሩ በተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና በሰባዊ መብት ተሟጋቾች ጭምር ሲነገር ቆይቷል።

ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ቆምቤ ጉግሳ በተባለ መንደር ነዋሪ እንደሆኑ ይናገራሉ። የ65 ዓመት አዛውንት ናቸው። ባለቤታቸው ደግሞ የ74 ዓመት አዛውንት መሆናቸውን ገልጸውልናል።

እንደ ወ/ሮ ሎሚ ገለጻ አራት ልጆች ነበራቸው። አቢቲ ደጃሳ የተባለ የ30 ዓመት አርሶ አደር ልጅ ነበራቸው። ደምሴ ደቻሳ ወይም ደሜ እያሉ በቁልምጫ የሚጠሩት የ22 ዓመት ልጃቸው ደግሞ "አዳማ ሄዶ ሥራ ፍለጋ ሲንከራተት ተይዞ ታስሯል" ይላሉ። የት እንደታሰረ ግን አያውቁም።

ንጉሴ ደቻሳ የተባለው ልጃቸው ደግሞ ከቤት ውስጥ ተደብድቦ ተወስዶ ወለንጪቲ ተወስዶ መታሰሩን ይናገራሉ።

ወ/ሮ ሎሚ በለቅሶ በታጀበ ድምጽ ረዳታቸው የ30 ዓመቱ ወጣት አቢቲ ደቻሳ ለስብሰባ ይፈለጋል ተብሎ ከቤታቸው ከተወሰደ በኋላ ጥቅምት 12 ቀን 2009 ዓ.ም አስክሬን እንደመጣላቸው ይናገራሉ።

የልጃቸው ለቅሶ ባይመጣና ቤታቸው ሐዘን ባይገባ ኖሮ ወለንጪቲ ታስሯል የተባለውን ልጃቸውን ንጉሴን ሄደው ይጠይቁት እንደነበር ገልጸዋል።

“አንዱን በሞት አጣሁ። አሁን አንድ ሰው አብሮኝ የለም። ቤቴ ባዶውን ቀርቷል። ደካማ ነኝ” የሚሉት ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ “የሞተው ልጄ ሞቷል፤ ያሉትን መልሱልኝ” ሲሉ ይጠይቃሉ።

የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ይህን በተመለከተ የደረሰን ሪፖርት የለም ብለዋል።

የኦሮመኛ ቋንቋ ዝግጅት ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋች።

ዝርዝርሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

“የሞተው ልጄ ሞቷል፤ ያሉትን መልሱልኝ” ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:00 0:00

አስተያየቶችን ይዩ (19)

XS
SM
MD
LG