ዋሺንግተን ዲሲ —
“ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ፍልሰተኞች፤ በአስቸኳይ በተሰሩት ማቆያ ቦታዎች ላይ ባለው የኑሮ ሁኔታ ደስተኞች ካልሆኑ አትምጡ” ብልዋቸው ሲሉ ትረማፕ በትዊተር ገልፀዋል።
ትረምፕ አያያዘውም ለችግሩ ተጠያቂ “የዲሞክራቶች መጥፎ የኢሚግረሽን ህጎች ናቸው” ሲሉ ዲሚክራቶችን ነቅፈዋል።
በህግ መወሰኛው ምክር ቤት የውሁዳን መሪ የሆኑት ቻክ ሹመር “እነዚ እኮ የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ወደ አሜሪካ የመጡ የሰው ልጆች ናቸው። አሜሪካ ማለት ምን እንደሆነች ማስታወስ የሚገብቸው ጊዜ ደርሷል” ሲሉ (አሜሪከ የፍልሰተኞችና የስደተኞች ሀገር ናት ለማለት ነው) ትራምፕ በትዊተር ላስተላለፉት መልእክት ምላሽ ሰጥተዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ