በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መጽሐፍ አዟሪዎች እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ገለጹ


የአዲስ አበባ መጽሐፍ አዟሪዎች ለደህንነታቸ በመስጋታቸው ማንነታቸው የተሸፈነ
የአዲስ አበባ መጽሐፍ አዟሪዎች ለደህንነታቸ በመስጋታቸው ማንነታቸው የተሸፈነ

መጽሐፍ አዟሪዎቹ በተለይ የተመስገን ደሳለኝ፣ የሙሉጌታ ሉሌና የዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሐፍ መሸጥ እንዳልቻሉ እነዚህን መጽሐፍትና ሌሎች የታሪክና የፖለቲካ መጽሐፍት ይዘው ሲገኙ እንደሚደበደቡ፣ እንደሚታሠሩና አንዳንዴም ለመለቀቅ ከደንብ አስከባሪዎች ጉቦ እንደሚጠየቁ ተናገሩ።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በበኩሉ ለአደጋ በሚያጋልጥ መልኩ በሕገ ወጥ መንገድ ሲሸጡ የተገኙ ይከለከላሉ እንጂ በተለየ መጽሐፍ እየተመረጠ እንዳይሸጡ የሚደረጉ የሉም ይላል።

የደራሲያን ማኅበር በበኩሉ አዟሪዎቹ ቀደም ባሉት ጊዜያት የተለያየ ችግር ሲደርስባቸው እየመጡ እንደሚያመለክቱ ችግሮቹ እንዲፈቱላቸው ጥረት እንደሚያደርግ ገልጾ አሁን በቅርቡ ተፈጠረ ስለተባለው ነገር በሪፖርት መልክ የደረሳቸው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

መጽሐፍ አዟሪዎች እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:11 0:00


XS
SM
MD
LG