በበርካታ ችግሮች ውስጥ በማለፍ ላይ ያለው የአውሮፕላን አምራቹ ኩባንያ ቦይንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴቪድ ካልሁን፣ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ከቦታቸው እንደሚነሱ ታውቋል።
ከአንድ ወር በፊት የአላስካ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በአየር ላይ ሳለ በሩ በመንገጠሉ፣ በኩባንያው ትርምስ ውስጥ ቆይቷል።
የጥር ወሩ ክስተት፣ ከአምስት ዓመታት በፊት በኢንዶኔዢያ እና በኢትዮጵያ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ተከስክሰው በአጠቃላይ 346 ሰዎች ከሞቱ ወዲህ የመጣና፣ ኩባንያው የአውሮፕላኖቹን ደህንነት በተመለከተ ያለበት ክፍተት ስጋት እንዲጨምር ያደረገ ነው።
የዋና ሥራ አስፈፃሚው ዴቪድ ካልሁን መልቀቅ፣ የአጠቃላይ የኩባንያው አስተዳደር ለውጥ አካል እንደሆነ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።
መድረክ / ፎረም