በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኒው ዮርክ ውስጥ ጥቁር ስደተኞች ስለዘር፣ ሀይማኖትና የቋንቋ መድልዎች ድምጻቸውን አሰሙ


በኒው ዮርክ ከተማ የመጠለያ ሥርዓትና በስደተኞች ድጋፍ ሰጭ አገልግሎቶች ውስጥ ዘር፣ ሀይማኖት እና የቋንቋ ልዩነቶችን በሚመለከት ስለተነሱ ጥያቄዎች የምስክር ቃል ለማድመጥ የተጠራ ጉባኤ በከተማ ምክር ቤት ለመታደም ወረፋ እየተጠባበቁ፣ ኒው ዮርክ
በኒው ዮርክ ከተማ የመጠለያ ሥርዓትና በስደተኞች ድጋፍ ሰጭ አገልግሎቶች ውስጥ ዘር፣ ሀይማኖት እና የቋንቋ ልዩነቶችን በሚመለከት ስለተነሱ ጥያቄዎች የምስክር ቃል ለማድመጥ የተጠራ ጉባኤ በከተማ ምክር ቤት ለመታደም ወረፋ እየተጠባበቁ፣ ኒው ዮርክ

በኒው ዮርክ ከተማ የመጠለያ ሥርዓትና በስደተኞች ድጋፍ ሰጭ አገልግሎቶች ውስጥ ዘር፣ ሀይማኖት እና የቋንቋ ልዩነቶችን በሚመለከት ስለተነሱ ጥያቄዎች የምስክር ቃል ለማድመጥ የተጠራ ጉባኤ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ በተካሄደበት በከተማ ምክር ቤቱ ፊት ለፊት ብዙ መቶ ጥቁር ሥደተኞች ታድመዋል፡፡

አዳራሹ የሚችለው በመቶዎች የሚቆጠሩ ብቻ በመሆኑ ከ1,500 የሚበልጡ የሚበዙት ከጊኒ የመጡ ስደተኞች የተሰበሰቡት የምክር ቤት አዳራሹን ተሻግሮ በሚገኘው ፓርክ ውስጥ ነው።

የከተማው ምክር ቤት የከተማ አገልግሎትን በሚጠቀሙ ስደተኞች ላይ የመረጃ አሰባሰብን ለማሻሻል እና የፌዴራል መንግስት የኢሚግሬሽን ማመልከቻ ክፍያ ማስከፈል እንዲያስቆም ወይም ለአመልካቾች የከፈሉትን እንዲመልስ እንዲከፍል የቀረበ ሃሳብ ላይ ተነጋግሯል።

አፍሪካውያን ስደተኞች የሚመጡት በአብዛኛው ምንም ልጆች ሳይኖራቸው ብቻቸውን ስለሆነ ውስን የሆነውን የመጠለያ ቦታ ለማግኘት ቅድሚያ አያገኙም”

የከተማው ምክር ቤት አባላት፣ ጥቁሮች ስደተኞች በብዛት ከመጠለያ እንደሚመለሱ፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እርዳታ እንደማያገኙ እና ከሌሎች በተለየ ለሃይማኖታዊ አምልኮ የጸሎት ስፍራ ማግኘት እንደሚቸገሩ የከተማው ባለሥልጣናት ራሳቸው ያመኗቸው አንዳንድ መረጃዎች እንዳሏቸው ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎች እንዲቀርቡላቸውም ጠይቀዋል፡፡

“አፍሪካውያን ስደተኞች የሚመጡት በአብዛኛው ምንም ልጆች ሳይኖራቸው ብቻቸውን ስለሆነ ውስን የሆነውን የመጠለያ ቦታ ለማግኘት ቅድሚያ አያገኙም” ሲሉ የከተማው ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

በከተማው ህግ መሠረት አዋቂዎቹ ስደተኞች ከ30 ቀን በኋላ ከመጠለያ እንዲወጡ ይገደዳሉ፡፡ ዕድሜያቸው ከ23 በታች የሆኑት ለሌላ መጠለያ ከማመልከታቸው በፊት መቆየት የሚችሉት ለ60 ቀናት ብቻ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የከተማው ምክር ቤት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር አሌሻ አቪሌ በሰጡት የምስክርነት ቃል ከ30 እስከ 60 ቀናት ያለው ገደብ ተመጣጣኝ ባልሆነ መንገድ በአብዛኛው የሚጎዳው ጥቁሮቹን ስደተኞች ነው ብለዋል፡፡

ድምጻቸውን ለማሰማት በቦታው ላይ የነበሩ አንዳንድ ስደተኞች የሥራ እና የመኖሪያ ቤት መረጃዎችን እንደሚሹ የተነገረ ሲሆን ብዙዎች በከተማ አስተዳደር የሚመራ የጤና መድህን ማግኘት እንደሚችሉ እንደማያውቁ ተጠቅሷል፡፡

የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር የሰጠው የኢሚግሬሽን እፎይታ እና የሥራ ፍቃድ መራዘም ውሳኔ የሚመለከተው ከተወሰኑ ሀገራት የመጡ ስደተኞችን ብቻ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG