የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፊሊፒንስ ከሚመጣባት ጥቃት ለመከላከለ አገራቸው ያላትን ቁርጠኝነት አሜሪካንን በመጎብኘት ላይ ላሉት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ገልጸውላቸዋል። ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች የተገናኙት በፊሊፒንስና በቻይና መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ በመጣበት ወቅት ነው።
ፕሬዚዳንቱ በተጨማሪም የፊሊፒንስን ጦር ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት አሜሪካ መደገፏን እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።
ሁለቱ መሪዎች የፊሊፒንስን ጸጥታ እና ሰራዊቷን ማዘመን በተመለክተ አዲስ የመከላከያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የፈላጭ ቆራጩ የቀድሞው የፊሊፒንስ መሪ ፈርዲናንድ ማርቆስ ልጅ የሆኑት የወቅቱ የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ፈርዲናንድ ማርቆስ ሁለተኛ፣ ትናንት ዋሽንግተን ላይ እንደተናገሩት፣ በደቡብ ቻይና ባህር እያየለ በመጣው ውጥረት ውስጥ አገራቸው ከፊት ትገኛለች።