በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በምርጫ ቅስቀሳ አክራሪ ጽንፈኞች ያሏቸውን ሪፐብሊካኖች ተቹ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትናንት ሰኞ የተከበረውን የሠራተኞች ቀን በመካከለኛው አጋማሽ የህዝብ እንደራሴዎች ምርጫ ለሚወዳደሩ ዴሞክራቶች ለመቀስቀስ፣ በፔንሰልቬንያ እና ዊስካንሰን በመጓዝ በአሜሪካ ፖለቲካ “ቀኝ አክራሪዎች” ባሏቸው ሪፐብሊካን ላይ የሚያሰሙትን ትችት አጠናክረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ “የከረረውን ርዕዮት” ይደግፋሉ ያሏቸውን ሪፐብሊካኖችን የተቹ ሲሆን አንዳንዶቹ ሪፐሊካን “በቁጣ መሞላትን ፣ ጥቃትን፣ ጥላቻንና ከፋፋይነትን በማንገብ ወደ ኋላ መሄድን መርጠዋል” ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ባይደን “አሜሪካን በድጋሚ ወደ ቀደመ ታላቅነቷ እንመልሳት” የሚለው አጀንዳና በዴሞክራሲ ላይ “ሥጋት ደቅነዋል” ያሏቸውን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ተከታዮች በመተቸት ባለፈው ሳምንት የተናገሩት “ሁሉንም ሪፐብሊካን የማይመለከት” መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሪፐብሊካንም የፕሬዚዳንቱን አስተያየት በከፋፋይነት ተችተዋል፡፡

ባይደን ማምሻው ላይ ከሠራተኞቹ ማህበራት ሥር ከታቀፉ ሠራተኞች ጋር ለመነጋገር ወደ ፒትስበርግ ፔንሰልቪኒያ ማምራታቸውም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG