በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ኮቪድ ያዛቸው


ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለኮቪድ-19 መጋለጣቸውን ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት አስታወቀ።

ፕሬዚዳንቱ ሙሉውን ክትባትና ሁለት ማጠናከሪያዎችን መውሰዳቸውን የቤተመንግሥቱ መግለጫ ጠቁሞ የበሽታው ቀላል ምልክት እንደሚስተዋልባቸውና የፓክስሎቪድ ህክምና መጀመራቸውን ገልጿል።

የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት /ሲዲሲ/ መመሪያ በሚያዝዘው መሠረት ፕሬዚዳንቱ ቤተመንግሥቱ ውስጥ ራሳቸውን ማግለላቸውንና ሁሉንም ሥራዎቻቸውን በተሟላ መልኩ እየተወጡ እንደሚቆዩ የቤተመንግሥቱ መግለጫ አክሎ አስታውቋል።።

የ79 ዓመቱ ባይደን ከኮሮናቫይረስ ነፃ መሆናቸው እስኪረጋገጥ ሥራቸውን የሚሠሩት ከሌሎች ተገልለው እንደሚሆን መግለጫው አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG