በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ታጣቂዎች ከ50 በላይ ሴቶች መግደላቸውን ፖሊስ ገለጸ


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን በሎ ጅጋንፎይ ወረዳ ነሐሴ 24 እና 25/2013 ዓ.ም ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት ከ50 በላይ ሴቶች መግደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ገለጸ።

ጉህዴን የተባሉ ታጣቂዎች በካማሺ ዞን አምስት ወረዳዎች ውስጥ ጥቃት ፈጽመው ሲቪሎችና የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው ኢንጂፈታ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ ሁኔታው ከክልሉ የመከላከል አቅም በላይ ከመሆኑ በፊት የፌደራል መንግሥት ድጋፍ ማድረግ አለበት ብለዋል።

በክልሉ መንግሥት ውንጀላ የቀረበባቸው አካላትን በስልክ ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ታጣቂዎች ከ50 በላይ ሴቶች መግደላቸውን ፖሊስ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:41 0:00


XS
SM
MD
LG