በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫ ቦርድ በአስቸኳይ አዋጁ ሳቢያ የቤኒሻንጉል ጉሙዝን የምርጫ ሂደት አቋረጠ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀውን፣ አገር አቀፍ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ፣ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ማጽደቁን ተከትሎ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ሰሌዳን እና ዝግጅትን ያቋረጠ መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

ምርጫ ቦርዱ፣ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን በአብዛኛው የአገራችን ክፍሎች አከናውኖ ማጠናቀቁን ገልጾ፣ በቢኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል በታህሳስ ወር ምርጫውን ለማከናወን የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ተግባራትን ማከናወን ጀምሮ እንደነበር አስታውሷል፡፡

XS
SM
MD
LG