ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግሥት ጋራ የሰላም ሥምምነት በመፈረም ከነታጣቂዎቻቸው ወደ ክልሉ የገቡ ሸማቂ ቡድን አዛዦች ከስምምነቱ ወዲህ በክልሉ ሰላም መስፈኑን ተናግረዋል።
የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ /ቤህነን/ ጦር መሪ አብዱልወሃብ መሀዲ ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጉህዴን/ ሊቀ-መንበር ግራኝ ጉደታ በበኩላቸው በአካባቢው አሁን ሰፍኗል ያሉትን ሰላም ለማስቀጠል እንደሚሠሩ ተናግረዋል።