ዋሺንግተን ዲሲ —
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ፕሬዚዳንት ትረምፕ በመጪው ሳምንት ከሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ተገናኝተው ከመነጋገራቸው በፊት ስለ ሀገራቸው ጥቅም ለመምከር ዛሬ ዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥትን ይጎበኛሉ።
የዩናይትድ ስቴትስና የጃፓን መሪዎች ለሁለት ሰዓታታ ያህል ከተነጋገሩ በኋላ ጋዜጣዊ ጉባዔ ያካሄዳሉ ተብሏል። ሁለቱ መሪዎች ስለ ሰሜን ኮርያና ስለ ንግድ እንደሚነጋገሩ ትረምፕ ዛሬ በትዊተር ገልፀዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ