በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ም/ቤት አባል ካረን ባስ የአጎዋ ውሳኔ ቀነ ገደብ እንዲራዘም ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ካረን ባስ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ካረን ባስ

የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ካረን ባስ የአፍሪካ ሃገራት በአሜሪካ ገበያ እንዲሳተፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያዘውን የአጎዋ ስምምነት የባይደን አስተዳደር እኤአ ከጥር 1 ቀን 2022 ጀምሮ እንዲቋረጥ ያስተላለፈው ውሳኔ እንዲራዘም የሚፈልጉ መሆኑን ዛሬ ባወጡት መግለጫ አስታውቁ፡፡

በተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ካረን ባስ፣ በመግለጫቸው እኤአ ህዳር ሁለት የተላለፈው የአጎዋ እገዳ ውሳኔ የኢትዮጵያ ህዝብና መዋዕለ ንዋይ ያፈሰሱ አሜሪካውያን ደክመው ያመጡትን የምጣኔ ሀብት እድገት ይቀለብሳል ብለዋል፡፡

እንዲሁም ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ለችግር ተጋላጭ የሆኑትን የህብረተሰ ክፍሎች ችግሮች ያባብሳል በማለት አክለዋል፡፡

ስለሆነም የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ወገኖች ይህን ግጭት ለማስቆም ተገቢውን እምርጃ ሁሉ እንዲወስዱ ፣ የሰብአዊ እርዳታን ለሚሹ ሰዎች እርዳታ እንዲለግሱ፣ ሰላምን ለማምጣት የሚያደርጉትን ድርድር ለመቀጠል በቂ ጊዜ እንዲያገኙ፣ የባይደን አስተዳደር በቂ ጊዜ እንዲሰጣቸው አሳስባለሁ ብለዋል፡፡

ካረን ባስ “እኤአ ጥር 1 2022 ተግባራዊ እንዲደረግ በድንገት የተላለፈው ውሳኔ ዜጎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ከማምጣት በቀር ለሰላሙ ምንም አማራጭ አይሰጥም” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG