በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ሊግ በዳካር ሴኔጋል ተጀምሯል


የአፍሪካ የቅርጫት ኳስ ሊግ 3ኛ ዓመት ውድድር በሳምንቱ መጀመሪያ በሴኔጋል ዳካር ተጀምሯል።

የዚህ ዓመት ፉክክር 12 ቡድኖች የሚሳተፉበት ሲሆን ቡድኖቹ በሦስት ምዕራፍ ተከፍሎ በሚደረገው ውድድር ላይ የላቀ ብቃት በማሳየት በሊጉ ታሪክ ውስጥ ስማቸውን በደማቁ ለማጻፍ ይፋለማሉ።

በመጀመሪያው ምዕራፍ የሰሐራ ምድብ የተደለደሉ ስድስት ቡድኖች ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት 15 ጨዋታዎችን ሴኔጋል በሚገኛው የዳካር አሪና ያከናውናሉ። ከሚመጣው የአውሮፓዊያኑ ሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 6 ባለው ጊዜ ደግሞ በናይል ምድብ የተደለደሉ 6 ቡድኖቸ በካይሮ ዶ/ር ሙስጠፋ ሀሰን የሰፖርት ማዘወተሪያ ይፉካከራሉ።

ከሁለቱ ምድቦች ልቀው የሚገኙ በአጠቃላይ 4 ቡድኖች ከግንቦት 21-27 በርዋንዳ ኪጋሊ አሪና በሚደረጉ ፉክክሮች ነጥረው ከወጡ በኋላ ግንቦት 27 ቀን የዓመቱ ውድድር ቻምፒዮን ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በአጠቃላይ 38 ጨዋታው የሚስተናገዱበት የዚህ ዓመት ውድድር ቅዳሜ ዕለት ሲጀመር የተገናኙት የሴኔጋሉ ኤኤስ ዱዋኔስ እና የአይቮሪ ኮስቱ አቢጃን የቅርጫት ከዋስ ክለብ ሲሆኑ አቢጃን የቅርጫት ኳስ ክለብ 76 ለ 70 በሆነ ውጤት ተጋጣሚውን ረቷል።

በቀጣዩ ቀን በተደረጉ ጨዋታዎች የሩዋንዳው ኢነርጂ ግሩፕ የናይጄሪያው ካዋራ ፋልከንስ የቅርጫት ኳስ ቡድን 64 ለ 48 አሸንፈዋል። በዚሁ ቀን የቱኒዚያው ኤኤስ ሞናስቲሪ የማሊውን ስታድ ማሊያንን 78 ለ68 በሆነ ውጤት ድል አድርጓል።

በአውሮፓዊያኑ 2021 በይፋ የተጀመረው የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ሊግ ቀዳሚ ቻምፒዮን የግብጹ ዛማሌክ ሲሆን፣ የባለፈው ዓመት አሸናፊ ደግሞ የቱኒዚያው ዩኤስ ሞናስቲር ነበር።

ጨዋታዎች እና ከጨዋታው ጋር የተገናኙ ትንታኔዎችን ለመስማት የቪኦኤ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ገጽን መጎብኘት አትዘንጉ።

XS
SM
MD
LG