በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ የቅርጫት ኳስ ሊግ አዳዲስ መረጃዎች


የአፍሪካ የቅርጫት ኳስ ሊግ አዳዲስ መረጃዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:41 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ሊግ የናይል ምድብ ጨዋታዎች ቀጥለዋል። በጉጉት የተጠበቀው የአምናው የሊጉ አሸናፊ የግብጹ ዛማሌክ እና ምድቡን ሲመራ የሰነበተው የአንጎላው ነዳጅ ድርጅት የስፖርት ክለብ (አትለቲኮ ደ ለዋንዳ የማሊ) ጨዋታ በዛማሌክ አሸናፊነት ተጠናቋል። ቅዳሜ ዕለት በተደረገው በዚህ ጨዋታ ዛማሌክ ተፎካካሪውን ቡድን 85 ለ 72 በሆነ ውጤት ነው የረታው። ይህ በሆነ በቀጣዩ ቀን የአንጎላው ክለብ አትለቲኮ ደ ለዋንዳ፣ የማሊ ፖሊስ ሰራዊት የቅርጫት ኳስ ክለብን 73 ለ60 አሸንፏል።

በዚያው ዕለት የኮንጎው ኢስፖይር ፉካሽ በግብጹ ዛማሌልክ 101 ለ92 ተሸንፏል። ዛሬ አመሻሹን፣ የማሊ የፖሊስ ሰራዊት የቅርጫት ኳስ ክለብ፣ ከደቡብ ሱዳኑ ኮብራ ቡድን ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል። የቪኦኤ የእንግሊዝኛው ጣቢያ ሁሉንም ጨዋታዎች ከካይሮ የዶክተር ሀሰን ሙስጠፋ የስፖርት ማዕከል በቀጥታ ያስተላልፋል።

XS
SM
MD
LG