በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባሕርዳር ላይ የተገደሉት ቁጥር ከተገለፀው በላይ ሊሆን እንደሚችል ተሰማ


ባሕርዳር
ባሕርዳር

ከአንድ ሣምንት በፊት በባህር ዳር ከተማ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 14 እንደሚደርስ የጥቃቱ ተጎጂዎች ተናገሩ።




please wait

No media source currently available

0:00 0:07:59 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ከአንድ ሣምንት በፊት በባህር ዳር ከተማ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 14 እንደሚደርስ የጥቃቱ ተጎጂዎች ተናገሩ።

የሟቾቹ ቁጥር በኋላ እራሱን እንዳጠፋ የተነገረውን ገዳዩን እንደማይጨምር ተገልጿል፡፡

በፌዴራል ፖሊስ አባል ፈቃዱ ናሻ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር አስራ ሁለት የቆሰሉ ደግሞ ሁለት መሆናቸውን ፖሊስ መግለፁ ይታወቃል።

የሟች ቤተሰቦች “ወንጀሉ ሲፈጸም ለማስቆም የሞከረ አካል አልነበረም” ሲሉም ያማርራሉ።

የከተማዋ የፀጥታ ባለሥልጣናት ግን በጉዳዩ ላይ መልስ ሊሰጡ ቃል ገብተዋል።

በሌላ በኩል በፖሊሱ ጥይት ቆስላ በሕይወት የተረፈችው እናና ማሩ ሰለ አደጋው የምታስታውሰውን ጉዳዮን ለመከታተል ወደ ባህር ዳር ለተጓዘው ዘጋቢአችን መለስካቸው አምሃ ገልፃለች።

ለዝርዝር ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG