“ከ2013 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ጋር በተያያዘ በተማሪዎች ለተነሳው ቅሬታ የተሰጠው ምላሽ አጥጋቢ አይደለም” ሲል የአማራ ተማሪዎች ማኅበር አሰታወቋል። በትምሕርት ሚኒስቴርም ሆነ በአማራ ክልል ትምሕርት ቢሮ የተሠጠው ምላሽ በንጽጽር የተሻለ ቢሆንም ጥያቄያቸው ግን እንዳልተመለሰ የማኅበሩ ኘሬዝዳንት እሸቱ ጌትነት ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ትምሕርት ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በ 2013 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አምጥተው ወደ ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ያልቻሉ ተማሪዎች በመምሕራን ኮሌጆች በመደበኛ የዲግሪ መርሃግብር እንደሚሰለጥኑ አመልክቷል ።