በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሚቺጋን ሦስት ተማሪዎች ተገደሉ ስድስት ቆሰሉ


ፖሊስ ድርጊቱ በተፈጸመበት አካባቢ
ፖሊስ ድርጊቱ በተፈጸመበት አካባቢ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚችጋን ክፍለ ግዛት ከዲትሮይት ከተማ 48 ኪሌሜትር ርቆ ኦክላንድ ውስጥ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት ውስጥ የ9ኛ ክፍል ተማሪ የሆነ የ15 ዓመት ወጣት በትናንትናው ዕለት በከፈተው ተኩስ ሦስት ተማሪዎችን ሲገድል ሌሎች ስድስት ተማሪዎችን ደግሞ ማቁሰሉ ተነገረ፡፡

ስሙ ያልተገለጸው ተጠርጣሪው ተማሪ፣ ምንም ጉዳት ያልደረሰበት ሲሆን፣ ከያዘው መሳሪያ ጭምር በቁጥጥር ስር መዋሉንና የድርጊቱም ምክንያት እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ ትናንት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG