አውስትራልያ፣ ታይላንድና ጃፓን፣ በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች እንዳሉባቸው ዛሬ ካስታወቁት ሀገሮች መካከል ይገኛሉ። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥም ለመጀመርያ ጊዜ፣ በቫይረሱ ምክንያት የሞተ ሰው መኖሩን፤ የሀገሪቱ የጤና ባለሥልጣኖች አስታቀዋል።
በሀገሪቱ ተጨማሪ የኮሮናቫይርስ በሽታ ሊኖር ቢችልም፣ “ፍርሀት እንዲኖር አያስፈልግም” ብለዋል ፕሬዚዳንት ትረምፕ።
የዩንይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሀገራቸው ኮሮናቫይረስን በሚመለከት፣ ሊከሰት የሚችል ማንኛውንም ዓይነት ችግር ለመቋቋም፣ ዝግጁ ናት ብለዋል። አሜሪካ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ፣ በቫይረሱ ምክንያት የሞተ ሰው መኖሩን፤ የሀገሪቱ የጤና ባለሥልጣኖች አስታቀዋል።
ትረምፕ ትናንት ዋይት ሀዋስ ቤተ-መንግስት በተደረገው ጋዜጣዊ ጉባኤ ሲናገሩ፣ በፊትም ቢሆን ታማሚ የነበሩ የ 50 ዓመት እድሜ ስው፣ ሌሊቱን ዋሽንግተን ክፍለ-ግዛት መሞታቸውን ገልጸዋል።
በሀገሪቱ ተጨማሪ የኮሮናቫይርስ በሽታ ሊኖር ቢችልም፣ “ፍርሀት እንዲኖር አያስፈልግም” ብለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል ሥራ አስኪያጅ፣ ሮበርት ሬድፊልድ፣ የሞቱት ሰው “ከሀገሪቱ ውጭ ተጉዘው እንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ የለም” ብለዋል።
የዋሽንግተን ክፍለ-ግዛት አስተዳዳሪ ጀይ ኢንስሊ፣ ትላንት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጅ ደንግገዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ