አዲስ አበባ —
የአፍሪካ ኅብረት የተሠረተበትን ሃምሣኛ ዓመት በዓሉን ቅዳሜ፣ ግንቦት 17/2005 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይና በሌሎችም የአፍሪካ ሃገሮች ዋና ከተሞች አከበረ፡፡
ኅብረቱ ከተመሠረተ አንስቶ ላለፉት ሃምሣ ዓመታት የዋና ፅሕፈት ቤቱ መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ በተከበረው ሥነ-ሥርዓት ላይ የበርካታ የአፍሪካ ሃገሮች መሪዎች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ-ሙን፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ እና ሌሎችም የአፍሪካ ወዳጆችና እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ሥነ-ሥርዓቱ በተለያዩ ውይይቶችና በፌስቲቫል የታጀበ እንደነበር የአዲስ አበባ ዘጋቢዎቻችን መለስካቸው አምሃና እስክንድር ፍሬው አመልክተዋል፡፡
የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የሆኑት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ንኮሣዛና ድላሚኒ ዙማም በተለያዩ መድረኮች ላይ ንግግሮችን አድርገዋል፡፡
የአዲስ አበባ የፀጥታ ጥበቃ የተጠናከረ እንደነበርም ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ለናይጀሪያ መንግሥት ባሰሙት ጥሪ የፀጥታ ኃይሎቻቹ ከቦኮ ሃራም ጋር በሚፋለሙበት ወቅት ሰብዓዊ መብቶችን እንዳይረግጡ ጥንቃቄ ማድረጋቸውን እንዲያረጋግጥ አሣስበዋል፡፡
ኬሪ ዛሬ ከናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ጋርም ለአጭር ጊዜ ተገናኝተው መነጋገራቸው ታውቋል፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሱዳንና በደቡብ ሱዳን መካከል ባለው የድንበር ፀጥታ ጉዳይ ላይም ከሁለቱም ሃገሮች ባለሥልጣናት ጋር ለአጭር ድርድር ተቀምጠዋል፡፡
ኬሪ በተጨማሪም ለዚሁ በዐል አዲስ አበባ ከሚገኙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ-ሙን ጋርም ተገናኝተው በሦሪያ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ሂደት፣ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክና በታላላቅ ሐይቆች አካባቢ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ወመያታቸውን አንድ የመንግሥታቱ ደርጅት ቃልአቀባይ አመልክቷል፡፡
ለተጨማሪ ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡