በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በዳያስፖራና ሀገር መሃል ድልድይ


ስለ አንዲት ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ የሚገፉ እናት፣ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ላይ ዘገባ የተከታተሉ ነዋሪነታቸው በካናዳ ያደረጉ ኢትዮጵያዉያን ታደጉዋቸዉ።

ወ/ሮ ሽቱ መሃመድ፣ ከጉራጌ ዞን ቄያቸዉን ለቀዉ ወደ አዲስ አበባ የመጡት ባዶ እጃቸዉን ነዉ። አልወለድሽም በሚል ሁለተኛ ባለቤታቸዉ ከቤት ሲያስወጡዋቸዉ በእጃቸዉ ምንም አልነበረም፣ እናም ከመጀመሪያ ትዳራቸዉ ያፈሩዋትን አንዲት ሴት ልጅ እዚያዉ ትተዉ አዲስ አበባ መጡ ወይዘሮ ሽቱ መሃነድ።

ዛሬ በአነስተኛ የጉልት ንግድ ስራ ተሰማርተዉ ከእጂ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ይገፋሉ። ገና በታዳጊነትዋ ከመጀመሪያ ባለቤታቸዉ ጋር የተዉዋትና ባለችበት ትዳር ይዛ ሶስት ልጆችን ያፈራችዉ ልጃቸዉ ግን የሁልጊዜም ናፍቆታቸዉ ናት። ስለስዋ ሲያወሩም እንባ ይቀድማቸዋል። ወደዚያዉ ለመጉዋዝ ዓይንዋን ለማዬት ያላቸዉ ጉጉትም በአቅም ማነስ ምክንያት ለረጅም ጊዜ አልተሳካም።

ከወራት በፊት በሕይወት በቀበሌ ላይ ያደረጉት ቃለ ምልልስ፣ አልበርታ ካናዳ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዉያን አድማጮችን ትኩረት ሳበ። ተገናኝተዉ በሚጫወቱበት አጋጣሚም ለሻይ የምናወጣዉን እንሰብስብ በሚል ወደ ኪሳቸዉ ገቡ። በድምሩ በኢትዮጵያ ብር ከ3 ሺህ 300 ብር በላይ አዋጡ። ከመካከላቸዉ ጸጋዬ ሽፈራዉ የተባሉ ለእህታቸዉ ሠርግ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ፣ ዘጋቢያችን እስክንድር ጋ ስልክ በመደወል ወይዘሮ ሽቱን እንዲያገናኛቸዉ ጠየቁ። ሁለቱ ወደ ወይዘሮ ሽቱ አመሩ። ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬዉ ዘገባ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG