በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት፥ በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ይዞታና መጪ ሁኔታዎች ዙሪያ፤


የገጠማቸውን የጤና እክል ተከትሎ፥ ሁለት ወራት ለተቃረበ ጊዜ አደባባይ ያልታዩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ያሉበት ቦታና የጤናቸው አያያዝ በውልና በይፋ አለመረጋገጡ የተለያዩ ወገኖችን እያወዛገበ ባለበት ባሁኑ ወቅት፤ አገሪቱ የምትከተለው፥ ወይም ልትከተል የምትችለው አቅጣጫ ምንነት ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።

ከዜጎች፥ እስከ ታዋቂ ምሁራንና ተንታኞች፤ ከፖለቲካው መድረክ ተዋናዮች እስከ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ድረስ የተለያዩ ወገኖች የበኩላቸውን የይሆናል ትንታኔዎች በመስጠት ላይ ናቸው።

በኢትዮጵያና በአካባቢው አገሮች መልከአ ምድራዊ ፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ላይ የነበራቸውን የጎላ ሚና ጨምሮ፥ የአቶ መለስ ሁኔታ የከሰታቸውንና እንዲሁም ሌሎች ለጊዜው ተጨባጭ መልስ ያላገኙ ጥያቄዎች መሠረት በማድረግ ከሁለት ምሁራን ጋር በወቅታዊው የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ የተካሄደ ውይይት ነው።

ተወያዮች ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በድህረ ምረቃ ትምህርት የሕብረተሰብ ፖሊሲ ትምህርት ክፍል መምህር ሲሆኑ፤ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ ደግሞ በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የኦሃዮ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የዴይተን ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ናቸው።

የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ቀጥሎ ያድምጡ፤

የውይይቱን ሁለተኛ ክፍል ቀጥሎ ያድምጡ፤

XS
SM
MD
LG