በይበልጥ በሴቶች ላይ የሚታይ፥ በየዕለቱ ለረዥም ሰዓታት መቆምን የሚጠይቅ የሥራ ሁኔታን ተከትሎ የሚከሰት ወይም የሚባባስ ቋንጃ አካባቢ የሚወጣ የእግር ላይ የደም ስር እብጠት በምን ይረዳል? ምን ዓይነት የህክምና አማራጮች አሉት?
በርዕሱ ዙሪያ ከአድማጮች ለደረሱን ተያያዥ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡን በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የWisconsin Madison University የጠቅላላ ቀዶ ህክምናና የደም ስሮች ቀዶ ሃኪሙ ዶ/ር ግርማ ተፈራ ናቸው።
ፕሮግራሙን ይከታተሉ።
በአመዛኙ በእግር ላይ አብጦ የሚታየው ይህ የደም ስር፥ በዘር ሊተላለፍ እንደሚችል የጠቆሙት የደም ስሮች ቀዶ ህክምና ባለ ሞያ፤ ባሉት የህክምና አማሮች በአግባቡ ከተረዳ አመርቂ ውጤት የሚገኝበት መሆኑንና እብጠቱንም ሆነ የህመም ስሜቱን ለመቀነስ የሚያስችሉ በህሙማኑ በራሳቸው የሚወሰዱ የመቆጣጠሪያ ዕርምጃዎች መኖራቸውንም ያስረዳሉ።