በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዘንድሮው የSEED ተሸላሚዎች አንዱ፤ ዶ/ር ረዳ ተክለሃይማኖት የመልካም ምግባር አረዓያው ሃኪም


ውይይት ክፍል አንድ፥ ሁለትና ሦሥት

የአካል ጉዳት የሚያስከትል ህመም ያደረባቸውን ከማከምና በበሽታቸው ምክኒያት የሚደርስባቸውን መገለል ከማስቀረት ባሻገር ራሳቸውን እንዲችሉ ማብቃት፤ ቁጥራቸው ከበዙ የሥኬት ሥራዎቻቸው ውስጥ ጥቂቱ ናቸው። የንፁህ ውሃ አቅርቦትን ጨምሮ የማኅበረሰቡን ሁለንተናዊ ህይወት እስከ ማሻሻል የደረሱ ክንውኖችንም ዕውን አድርገዋል።

በእንግሊዝኛው ምህፃረ ቃል SEED በመባል የሚታወቀውና በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት («ማኅበረ-ግዩራን ዘረ ኢትዮጵያ፤» በአማርኛ ሙሉ ሥያሜው፤) በዘንድሮው 19ኛው ዓመታዊ ሥነ ሥርዓቱ ለሽልማት ካበቃቸው አንዱ ናቸው፤ ዕውቁ የነርቭ ሃኪም ፕሮፌሰር ረዳ ተክለኃይማኖት።

ሥፍራው፥ ቡታጅራ ኢትዮጵያ፤ ድርጅታቸው ደግሞ «ግራር ቤት፥ ተሃድሶ ማኅበር፤» ይባላል።

የፕሮፌሰር ረዳን የተወደሰ ሥራ በቅርበት የተከታተሉትንና የድርጅቱን አገልግሎት ተጠቃሚዎች የምስክርነት ቃል ያባሰቡትንና ለሽልማቱም ያጯቸውን አቶ ጴጥሮስ አክሊሉን ጨምሮ ከሁለቱ እንግዶች ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ በሦሥት ተከታታይ ክፍል ቀርቧል።

እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።

ውይይት ክፍል አንድ

ውይይት ክፍል ሁለት


ውይይት ክፍል ሦሥት

XS
SM
MD
LG